በድሬደዋ አስተዳደር የእጩ አሽከርካሪዎች የፅሁፍ ፈተናን ከአማርኛ በተጨማሪ በኦሮመኛ እና በሱማለኛ ቋንቋዎች ለመስጠት የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽቤት አስታወቀ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሁለቱን ቋንቋዎች የፅሁፍ ፈተናዎች የትርጉም ስራ ከድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ተረክቧል፡፡ በርክክብ ስነስረአቱ ላይ የትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በጽ/ቤቱ ከዚህ ቀደም የእጩ አሽከርካሪዎች የፅሁፍ ፈተና ይዘጋጅ የነበረው በአማርኛ ቋንቋ ብቻ መሆኑን ተከትሎ በርካቶች ፈተናውን ተረድቶ ከመስራት አንፃር ሰፊ ክፍተት እንደነበር አስታውሰው በዚህም በተለይ የተግባር ፈተናውን ባግባቡ የሰሩ እጩ…


