የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች አለም አቀፍ ማህበር” ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ::
በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ በተካሄደው የድጋፍ መርሀግብር ላይ ወ/ሮ ሜላት ብርሀኔ ማህበሩን በመወከል ባደረጉት ንግግር በአሜሪካና በአውሮፓ በሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች የተመሰረተው ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል:: በዛሬው ድጋፍም ከተለያዩ የአስተዳደሩ የከተማ ቀበሌዎች ለተመረጡ 200 አቅመ ደካማ የእስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በዓል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 1ሺህ ብር…


