መልዕክተ ድሬ 702
ልዩነቶቻችን ውበት እና መብቶቻችን እንጂ የግጭት መንስኤዎች ሊሆኑ አይገባም! ልዩነቶች ከነባራዊ ሁኔታዎቻችን አሊያምከዝንባሌዎቻቻንና ከፍላጎቶቻችን የሚመነጩ የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው ፡፡ ከዚህ አንጻር ምንም ዓይነት ልዩነቶች ከተፈጥሯዊ ማንነታችንና ከዕምነታችን ስለሚመነጩ በአስተሳሰብና በተግባራችን ሊገለጡ ይችላሉ ፡፡ እነዚህ ልዩነቶቻችን አንዳንዶቹ ገና ከጠዋቱ ስንወለድ ጀምሮ አብረውን የነበሩ በመሆናቸው ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከጊዜ በኋላ በመኖር ሂደት አምነገንባቸው የተቀበልናቸው ስለሆኑ ከማንነታችን ጋር…


