የአስተዳደሩ የግብርና ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለ38 ገጠር ቀበሌዎች የልማት ጣቢያ ሰራተኞች እና ለ4 ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች የስርአተ ምግብና ስለ ጓሮ አትክልት እንዲሁም የምግብ እጥረት በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡
የግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የስርአተ ምግብ ተጠሪ ወ/ሮ ሽልማት እንግዳ የስልጠናውን አስፈላጊነት አስመልተው በተናገሩት ንግግር በ2030 ዓ.ም እንደ ሀገር ብሎም በአስተዳደራችን ከተቀመጠው አንዱና ዋና አላማ በህጻናት መቀንጨር ለመግታት ሲሆን ግንዛቤ መፍጠር ማዳበር ሂደት አንዱና ዋንኛው መሆኑን በመግለፅ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት በተለይም በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን ግንዛቤ ለመፍጠር የስልጠናው ተሳታፊዎች የድርሻችሁን መወጣት…


