ህዝቡ የኮቪድ 19 ጫና ውስጥ ባለበት ሁኔታ የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ መደረጉ የህዝቡን ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ተባለ ::

    በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የግል፣ የማብረሰብ/የህዝብ እንዲሁም የእምነት ተቋማት ትምህርት ቤቶች በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ መንግስት ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስ የሚያደርገውን ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽዎ በማበርከት የተማረ ዜጋ በማፍራት ከፍተኛ እገዛ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች በሚሰጡት የትምህርት አገልግሎትም ከየተማሪው ክፍያ በመቀበል ትምህርትን በማዳረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከክፍያ ሂደቱ ጋርም ተያይዞ በአስተዳደሩ በተለያዩ በግል፣ በማህበረሰብ/በህዝብና…

    Read More

      በድሬዳዋ አስተዳደር ከ 725 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድና የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

      ግንባታዎቹም ለከተማዋ ለነዋሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተገልፃል፡፡ መንገድ ለአንድ ሀገር እድገት ብሎም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በድሬዳዋ አስተዳደር ከ 725 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ የሚገኙ አዳዲስ መንገዶችና ነባር መንገዶችን የመጠገን ስራ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በከተማዋ ላይ ጎርፍ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ ጋር ተያይዞ ይህንንም ለመከላል ይቻል…

      Read More

        የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442 ኛው የረመዳን የፆም ወር በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

        ፆሙ የእዝነት:የአብሮነት : የተቸገሩትን የምንረዳበት እና የበረከት ፆም እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን በዚህ የፆም ቀናት በሃገራችን ብሎም በከተማችን አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ ምክሮችን ሳንዘናጋ እንተግብራቸው። ረመዳን ከሪም

        Read More

          6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ መራጩ ህዘብ ተገቢውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እና የዜጎችን ተሳትፎ በምርጫው ላይ እንዲኖር በበጎ ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ፡፡

          ያለ ዜጎች ተሳትፎ እውነተኛ ዴሞክራሲና፣ ሕገ መንግስቱን እውን ለማረግ እንደማይቻል ሁሉ ከቅርብ ወራት በኋላ የሚካሄደውን 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተሳትፎ የዳበረ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በእንደዚህ ዓይነቶቹ ስልጠናዎች አማካኝነት ዜጎችን ማስተማር የምርጫው ውጤት ግልጽና በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲሆን፡፡ የስልጠናውን ያዘጋጀው ምስራቃዊ የዕድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር ከINITIATIVE AFRICA በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ 6ተኛው ዙር አገር…

          Read More

            በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በተሻለ መልኩ ለመስራት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ::

            በድሬዳዋ አስተዳደር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 21 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በህብረተሰቡ ተሳትፎ ኦጀንሲ ኃላፊነትና በዘጠኙም የከተማ ቀበሌዎች ቅንጅት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ የልማት ስራዎች በውጤት ለማጠናቀቅም መንግስት ከሚመድበው በጀት በዘለለ ከህብረሰተቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በዓይነት ድጋፍ እንዲደረግ ይጠበቃል፡፡ ይህንን መሰረት ባደረገ መልኩ በቀበሌ 05 አስተዳደር በህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ሲቀርብ የነበረው ቀርሳ ተራ የገበያ ማዕከል አካባቢ የተገነባው…

            Read More

              በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች እራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ከመጠበቅ ባለፈ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

              ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታ በድሬዳዋ አስተዳደር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ፡፡ በሽታው በሀገራችን ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በድሬዳዋ አስተዳደር 32 ሺህ 209 ለሚሆኑ ሰዎች የናሙና ምርመራ በማድረግ 3 ሺህ 718 የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ድረስም ከበሽታው ጋር ተያይዞ በከተማዋ የ 45 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በሀገር አቀፍ ደረጃ…

              Read More

                ለአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የታዳጊ ህፃናት የሰላም ዕውቀት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ::

                በድሬደዋ አስተዳደር የምስራቅ ጀግኖች ት/ቤት ተማሪዎች በሀገራቀፍ የመጀመሪያው የሰላም ቀን ባከበሩበት ስነስርዓት ላይ የተገኙት የድሬ ደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ባደረጉት ንግግር ለአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የታዳጊ ህፃናት የሰላም ዕውቀት ከፊተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በየትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎቻችን ሰላምና አብሮነትን ፣ መብትና እና ግዴታን በአግባቡ እንዲረዱ ለማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን የሰላም እና የአብሮነት…

                Read More

                  በነገው ዕለት በአስተዳደራችን የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን ዙሪያ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ፡፡

                  በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት የሚካሄደው 4ኛ ዙር የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጫዋታዎች ከነገ መጋቢት 29/2013ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ሳምንታት ይካሄዳል፡፡ ይህንን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኩሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡ በድሬዳዋ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማዘጋጀትና ጨዋታን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአስተዳደሩ…

                  Read More