ስፖርታዊ ውድድሮች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን በማሻሻል የሀገር ልማት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዲኖረው ከማድረግ በዘለለ ለወጣቶችም የስራ እድል እንዲፈጥር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ለሚገኘው የቤትኪንግ ኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መሳካት የጎላ ሚና ለነበራቸው አካላት የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ የ 2013 የቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 4 ተኛው ዙር የቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ 13 ክለቦች ተሳታፊ ሆነው ውድድራቸውን እያካሄዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ የሚዲያ…

    Read More

      የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች አለም አቀፍ ማህበር” ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ::

      በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ በተካሄደው የድጋፍ መርሀግብር ላይ ወ/ሮ ሜላት ብርሀኔ ማህበሩን በመወከል ባደረጉት ንግግር በአሜሪካና በአውሮፓ በሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች የተመሰረተው ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል:: በዛሬው ድጋፍም ከተለያዩ የአስተዳደሩ የከተማ ቀበሌዎች ለተመረጡ 200 አቅመ ደካማ የእስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በዓል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 1ሺህ ብር…

      Read More

        ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በሀገር ውስጥ አቅም በማምረት ለኮቪድ 19 ፅኑ ህሙማን ለማድረስ እያደረገ ያለው ጥረት እየተሰናከለ መሆኑን ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱሰትሪ ኃ/የተ/የግ ማህበር አስታወቀ፡፡

        መቀመጫውን ድሬዳዋ ያደረገው ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኢንጅነሪንግ ክፍል ማናጀር ኢንጅነር ምንያህል ደበበ እንደተናገሩት ድርጅቱ በአሁን ሰአት የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘውን የኮቪድ 19 ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ፡፡ ድርጅቱ ወርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛ እጥረት የሚታይበትን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (መካኒካል ቬንትለት) በሀገር ወስጥ በራስ አቅም ለማምረት ሰፊ ግዜና በጀት…

        Read More

          አራቱ የገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች በድጋፍ የተበረከተላቸውን ዘይት ፤ፓስታ እና ሩዝ ተረከቡ ፡፡

          በዛሬው እለት በአራቱም ገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች ተገኝተው የምግብ ሸቀጣሸቀጦቹን ያስረከቡት የድሬዳዋ አስተዳዳር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ እና የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ውቢት በፍቃዱ ናቸው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የምግብ ሸቀጦቹን ለፖሊስ አባላቱ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ፖሊስ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ከቻለ የህዝብን አመኔታ መፍጠር ይችላል ብለዋል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር…

          Read More

            የብልፅግና ፓርቲ የዘመድ ጥየቃና የመደጋገፍፍ ስነ_ስርዓት በቀበሌ 08 አካሄደ።

            ድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በህጅራ አቆጣጠር 1442 ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክኒያት በማድረግ የዘመድ ጥየቃ እና አቅመ ደካማዎችን የመጠየቅ የዝምድና ማጠናከር ስነ_ስርዓት በቀበሌ 08 በተለምዶ ለገሀሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተካሄዷል። በዝግጅቱ ላይ በድሬደዋ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳት ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ጨምሮ የሊጉ አባላትና የፓርቲ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በቀሌዉ የብልፅግና ፓርቲን ወክለዉ የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዬች…

            Read More

              በድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ሜዳ በብልጽግና ፓርቲ አዘጋጅነት የከተማውን ወጣቶች ያሳተፈ የቁንጅና ውድድር ተካሄደ::

              የቁንጅና ውድድሩ የብልጽግና ፓርቲ የቅስቀሳ ስራ አካል ሲሆን በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች የብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ አምስት አመት ሊሰራቸው ያሰባቸውን እቅዶች በተመለከተ ወጣቶች በተረዱት አግባብ የፈጠራ ክህሎታቸውን ተጠቅመው ጥበባዊ ውበትን በተላበሰ መልኩ ለታዳሚ አቅርበዋል፡፡ በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑት ወጣቶች በተላያዩ ክበባት ተሳታፊ የሆኑና በፍቃደኝነት በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን የፈቀዱ ወጣቶች በውድድሩ መሳተፋቸውን የድሬደዋ ብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት…

              Read More

                ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የቢሮ ስብሰባ እንዲጠራ ሀሳብ አቀረበች::

                ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የተከሰተውን አለመግባባት ለመፍታት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የቢሮ ስብሰባ እንዲጠራ ሀሳብ አቀረበች። የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርን ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀ-መንበር ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ትሼኬዲ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ስብሰባ እንዲጠሩ መጠየቅ እንደሚገባ ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የተጻፈው ደብዳቤ ያትታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሱዳን ጠቅላይ…

                Read More

                  በምክር ቤቱ አሰራር ላይ ተቋማዊ ሪፎርም እያደረገ እንደሚገኝ የፌዴሬሽን ም/ቤት አስታወቀ::

                  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቤቱታዎች አቀራረብ፣ በውሳኔ አሰጣጥ፣ አፈፃፀምና ጥራት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን እንደሚፈታ የታመነበት ተቋማዊ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። የህገ መንግስት የበላይነት፣ ዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ አንድነት፣ ውጤታማ የሀብት ክፍፍል እና ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም የተቋሙ የሪፎርም ትኩረቶች መሆናቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል። ምክር ቤቱ ከክልል አፈጉባኤዎች፣ ከጠቅላይ አቃቢ ህግ እና ከህገ መንግስት…

                  Read More

                    በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ለአራቱ ገጠር ፖሊስ ጣቢያ አባላቶች ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶች ድጋፍ ተደረገ፡፡

                    የዋጋ ግምታቸው ከአንድ መቶ ሺብር በላይ የሚሆኑ ሀምሳ ኪስ ሩዝ፤ሀምሳ ደርዘን ፓስታ እና ሀምሳ ፍሬ የምግብ ዘይት ፤በገጠር ፖሊስ ጣቢያ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ አባላት አዲል ጠቅላላ አስመጪ ድጋፉን ማድረጉ ታውቋል፡፡ የአዲል ጠቅላላ አስመጪ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አዲል ይሳቅ ርክክቡን ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከለውጡ በኋላ የከተማውን ሰላም እና ጸጥታ በማረጋገጥ ረገድ…

                    Read More

                      የትራንስፖርት መጨናነቁን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

                      ድሬዳዋ ከተቆረቆረች ከ115 ዓመት በላይ ሆኗታል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች እድገትን አስመዝግባለች፡፡ ከነዚህ ዘርፎች ውስጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን በአግባቡ ሊያቀላጥፍ የሚችለው የመንገድ መስመር ዝርጋታ ስራ ዋነኛው ነው፡፡ እንደአስተዳደር ከዚህ አንጻር በርካታ ስራዎች የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይም የከተማዋን ዕድገት ሊሸከምና የትራንስፖርት መጨናነቁን ሊያቃልል የሚችል ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡ የፈረንሳይ መንግስት ባደረገው እገዛ በመጣ ድርጅት በተለያዩ…

                      Read More