ዛሬ በድሬደዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የዘጠኝ ሰው ህይወት ማለፉን ተገለፀ::

    አደጋው ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ ሸመንተሪያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መከሰቱን የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዲቪን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ባንታለም ግርማ ተናግረዋል ። አክለውም ከጠዋት ሁለት ሰአት ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ሰዓታት ዝናብ ሲጥል መቆየቱን በዚህም ሳቢያ እርዝመቱ 50 ሜትር የሆነ የግንብ አጥር በሶስት ቤቶች ላይ ተደርምሶ ከቀኑ ስድስት ከሀያ…

    Read More

      የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ባስተላለፉት የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው በዓሉን በመደጋገፍና በመረዳዳት ልናከብረው እንደሚገባ ጠቆሙ::

      የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ባስተላለፉት የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ አያይዘውም በዓሉ በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ እንዲከበር ምኞታቸውንም ገልጸዋል፡፡ አክለውም እኛ ክርስቲያኖች በመገረፉ ቁስል የተፈወስን ከመከራ ስቃይ የዳንበት፤ ከወደቅንበት የተነሳንበት ልዩ በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የተረሱ፣…

      Read More

        የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገለጹ::

        የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ ባስተላለፉት የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክታቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ከንቲባው አያይዘውም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን የተመኙ ሲሆን ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ሲያከበር በኢትዮጵያዊነትና በድሬዳዋዊነት እሴቶቻችን የተቸገሩን የምናስብበት፣ የምንደጋገፍበትና በጋራ የምናከብረው መሆን ስላለበት የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይገባል…

        Read More

          በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በህግ ማስከበር ተሳትፎ ጉዳት ደርሶባቸው በምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ለማበረታታት ያለመ ፕሮግራም ተካሄደ ።

          የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ከሀገር ውስጥ ብሎም ከሀገር ውጪ የሚቃጣበትን ጥቃት ከመመከት ባለፈ ቀን ከለሊት የሀገሩን ዳር ድንበር በማስከበር ላይ ይገኛል ። ይህንንም ተከትሎ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው የህግ ማስከበር ተልእኮ ላይ ተሳትፈው ጉዳት ደርሶባቸው በምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ማበረታታትና ከጉዳታቸውም አገግመው ወደ ግዳጅ እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ይቻል ዘንድ እንዲሁም የፌደራል…

          Read More

            በመላ ድሬዳዋ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ዕለተ ስቅለት በድምቀት ተከበረ::

            በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የካቲት መጨረሻ ላይ የተያዘው የአብይ ጾም በጾምና በጸሎት አምላክን በመለመንና በመማጸን አሳልፈው ጾሙ ሊገባደድ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ በተለይም በአብይ ጾም የመጨረሻው አርብ ከሌላው ቀናት ለየት የሚያደርገው ኢየሱስ ክርስቶች በመስቀል ላይ እሱ ሞቶ ለመላ የሰው ልጆች ህይወት የሰጠበት ዕለት በመሆኑ ቀኑን በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ስለሆነም ይህን በማሰብ በመላ…

            Read More

              የድሬዳዋ አስተዳደርን ጨምሮ የምስራቅ ሀረርጌ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሶስት ቀናት ከፍተኛ የሆነ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተገለፀ ።

              ነዋሪው ህብረተሰብም ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባም ተገልፃል ። የድሬዳዋ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት በከተማችን ድሬዳዋ ብሎም በአጎራባች ክልሎች አደጋ ከመድረሳቸው አስቀድሞ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ለአደጋው ቅድመ መረጃ ኖሯቸው ለአደጋው ተጋላጭ እንዳይሆኑ ብሎም ሊደርስ ከሚችል ጉዳት እራሳቸውን እንዲከላከሉ ተገቢውን መረጃ ይሰጣል ። ከዚህም ባለፈም ይህንን ስራ ለሚሰሩ አስፈፃሚ ሴክተር መስሪያ ቤቶች…

              Read More

                በቀበሌ 06 አስተዳደር 200 ለሚሆኑ ችግረኛ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ::

                የቀበሌ 06 አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም በአካባቢው ላይ ለከተማ ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች በቀበሌው ከሚገኙ ባለሀብቶችና የንግድ ማህበረሰቦች ባሰባሰቡት ገንዘብ 200 ለሚሆኑ ለአካባቢው ችግረኞች የታለቁን ረመዳን ጾምና የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በድጋፍ መድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የብልጽግና…

                Read More

                  በድሬዳዋ አስተዳደር ፀረ-ሰላም ሀይሎች ገብተዋል ተብሎ የሚናፈሱ ወሬዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ መሆናቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።

                  ፖሊስ ኮሚሽኑ ከምን ጊዜውም በላይ የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተገልፆል ። የድሬዳዋ አስተዳደር የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና እምነት ተከታዮች በጋራ በአንድነት ተቻችለውና ተከባብረው እንደሚኖሩባት ይታወቃል ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የከተማዋን በጋራ የመኖር እሴትን ለማደፍረስ የሚጥሩ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ከተማዋ እንደገቡ ተደርጎ ያልተጨበጡና ፍፁም ከእውነት የራቁ መረጃዎችን ህብረተሰቡ ዘንድ እየተሰራጩ ይገኛሉ ። እነዚህም መረጃዎቹ…

                  Read More

                    በሁሉም ከተማ ቀበሌዎች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአስተዳደሩ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

                    ከ2014-2016ዓ.ም የድሬዳዋ ከተማ የካፒታል ኢንቨስትመንት ዕቅድ (CIP)ዝግጅት አስመልክቶ የከተማው ህብረተሰብ እና የባለድርሻ አካላት ጋር በእቅድ ዝግጅቱ እንዲካተቱ የሚያስፈልጉና አዲስ ኘሮጀክቶች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡ ፡ በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ከፕሮጀክቶቹ መካከል ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥረው የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራን ጨምሮ የጠጠር መንገድ፣ የጎርፍ መከላከያ ግንብ፣ አዲሱ ቄራ፣ የመንገድ መብራት፣ ፓርክና የመንገድ አካፋይ ግንባታና አረንጓዴ…

                    Read More

                      የተፈጠረውን የኦክስጂን እጥረት ለማቃለል ባለሀብቶች ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ፡፡

                      በድሬዳዋ ጤና ቢሮ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ለሆነው የፈረንሳይ ሆስፒታል ክሮምቶ ማኑፋክቸሪንግ ፒልሲ 50 ኦክስጂን የተሞላባቸውን ሲሊንደሮች በድጋፍ አበርክቷል፡፡ በድጋፍ አሰጣጡ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ዕለት ተዕለት የኮቪድ-19 ስርጭት መጠን መስፋፋቱን ተከትሎ በአስተዳደራችን የህሙማን ቁጥርም በመጨመሩ ምክኒያት የተከሰተውን የኦክስጂን እጥረት ግምት ውስጥ በማስገባት ክሮምቶ ማኑፋክቸሪንግ ፒልሲ ላደረገው የኦክሲጂን ሲሊንደሮች ድጋፍ ምስጋናቸውን…

                      Read More