የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን እና ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር 27,380,069.46 ብልጫ እንዳላው አስታወቀ::

    የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ ዛሬ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ወር እና የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከመንግስት ታክስ እና ከመዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር140,865,471.36 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 137,402,956.20 መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት የወሩን የእቅዱን 97.54በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ዕቅድ አፈፃፀም ከ2012…

    Read More

      ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ የአፍጢር ፕሮግራም አካሂደዋል ።

      ከአፍጢር ፕሮግራሙ ጎን ለጎንም ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደርጓል ። 1442 ተኛውን ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በ 06 ቀበሌ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት የአፍጢርና ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የድጋፍ ፕሮግራም አካሂዷል ። በስነ-ስርአቱ ላይም የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ሻኪር አህመድ በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት…

      Read More

        የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ ጀመሩ::

        የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ መጀመራቸውን የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡ ሁለቱ የውሃ ማስተንፈሻዎች ስራ የጀመሩት ግንባታቸው ተጠናቆና የሙከራ ስራ ተከናውኖባቸው መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ገልፀዋል፡፡ ስራ የጀመሩት ማስተንፈሻዎቹ አጠቃላይ ዓመታዊውን የዓባይ ውሃ ፍሰት የማሳለፍ አቅም እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡ ማስተንፈሻዎቹ በግድቡ ሙሌት ወቅት የዓባይ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ ሀገራት…

        Read More

          የአስተዳደሩ ብሔራዊ የሥርዓተ-ምግብ ተግባሪዎች ለሥርዓተ-ምግብ ትግበራው በጋራ በመስራት የመቀንጨር ችግርን ሊቀንሱ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

          በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤና ማበልፀግ ኬዝ ቲም የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር የምግብና ሥርዓተ-ምግብ የአፋፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ አካሄዷል፡፡ በተዘጋጀው የአፋፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ መስሪያቤቶችና፣ ድጋፍ ሰጪዎች የአስተዳደሩ ብሔራዊ የሥርዓተ-ምግብ ተግባሪዎች የተገኙ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተግባሪ ተቋማት እንዲሁም በጤና ቢሮ…

          Read More

            በቀበሌ 02 ነዋሪ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት የምርጫ ቅስቀሳ በሰልፍ አካሄዱ።

            በድሬደዋ አስተዳደር በ 9 የከተማ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ዛሬ ሚያዚያ 10/2013 ዓ.ም የብልፅግና ፓርቲን ያላቸውን ድጋፍ የምርጫ ቅስቀሳ በሰልፍ አካሄዱ። በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ሰልፈኞቹ በቀበሌው በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር የድጋፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች አስተላልፈዋል።

            Read More

              በድሬዳዋ አስተዳደር በ 350 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለሚገነባው የብረታ ብረትና ሲሚንቶ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የመሰረት ድንጋይ በዛሬው እለት ተቀመጠ ።

              በድሬዳዋ አስተዳደር ከመልካ ጀብዱ ወጣ ብሎ በኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ በ 103 ሄክታር መሬት ላይ በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግና በዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያዎች በሽርክና ለሚገነባው የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና ምክትላቸው አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የንግድ…

              Read More

                የቴክኖሎጂ ፈጠራና ክህሎት ባለቤቶችን ማበረታታት ዘርፉ ለአገር ኢኮኖሚ እድገት ሊያበረክት የሚችለውን ሚና እንደሚያሳድገው ተገለጸ::

                በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ሁለተኛው የቴክኖሎጂ ፈጠራና ክህሎት ውድድር እንደአስተዳደር ተወዳድረው በተለያዩ ዘርፎች ድሬደዋን ለመወከል የተመረጡ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል። በሽልማት ስነስረአቱ ላይ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቭስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር ጁሃር በአለም ላይ ያደጉ አገራትም ሆነ በማደግ ላይ ያሉ አገራት የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ክህሎት የእድገታቸው ዋነኛ…

                Read More

                  በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

                  6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ ነፃና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆንና ምርጫውን በበላይነት በማሸነፍም የህዝብ ተወካዮች መቀመጫ የማግኘት ግቡን እውን ለማድረግ በሚያግዝ መልኩ ዛሬ ለፓርቲው የታችኛው መዋቅር አመራርና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው ። በስልጠናውም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸው አቋሞች ፣ ባለፉት 3 አመታት ፓርቲው ያሳካቸው ድሎችና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሰነቀው ህልም ለአባላቱ በሰፊው ተገልጿል…

                  Read More

                    በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገቡ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ::

                    አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገቡ ባለሃብቶች ምርቶችን በማምረት ለውጪ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ። ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ፓርኩ ለ2 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ባለፉት ስድስት ወራትም 6 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉን አቶ ካሚል ተናግረዋል። ወደ ስራ…

                    Read More