Amharic
የከንቲባ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት እቅድ የፊርማ ስነ- ሰርዓት አከናወነ
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ከስራ ክፍሎችና ከተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮች ጋር የፊርማ ሰነ-ስርዓት አከናውኗል። የ2018 በጀት አመት እቅድ ከጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ጋር የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮች የፊርማ ሰነ-ስርዓት አከናውኗል። በፊርማ ስነ-ስርዓቱ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን የተከናወኑ አበረታች ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ያሉ ውስንነቶች ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የወረዳ 04 ተመራጮች የመስክ ምልከታ አደረጉ
በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የወረዳ 04 አስተዳደር የህዝብ ተመራጮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የህዝብ ውክልና መወጣት የውይይት መድረክ በጠዋቱ መርሃ-ግብር ያከናወኑ ሲሆን፤ በከሰዓት ውሎ ደግሞ በወረዳው የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በዚህም የገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያንና ጤና ጣቢያን አጠቃላይ የስራ ሂደት የተመለከቱ ሲሆን ከተቋማቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋርም በአጠቃለያ በተቋማቱ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ…
በአፈር እና ውሀ ጥበቃ የተሰሩ ስራዎች ተጎበኙ
የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር ልማት ሴፍቲኔት በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የሚመክር ውይይት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ በዛሬው እለት መጀመሩ ይታወሳል ። በጠዋቱ መርሀ-ግብርም በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን በመቀጥልም የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል ። ጉብኝቱም በልማታዊ ሴፍቲኔት በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራ የተሰሩ ስራዎችን በዋሂል ክላስተር ሁሉልሞጆ ገጠር ቀበሌ እንዲሁም በአሰሊሶ…
ባለፍት አመታት በምግብ ዋስትና ነዋሪውን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ
በድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር ልማት ሴፍቲኔት በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የሚመክር ውይይት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ በዛሬው እለት ተካሂዷል ። በምግብ ዋስትና ፕሮግራም በተለይም በአትክልት እና ፍራፍሬ ፣ በእንስሳት ሀብት ፣ በወተት ሀብት ፣ በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራ በርካታ ስርልዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ…
በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ወረዳ አራትን ወክለው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት የህዝብ ውክልና መወጣት የውይይት መድረክ አካሄዱ
በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 4 አስተዳደር ማህበረሰብን ወክለው የአስተዳደሩ ምክር ቤት ተመራጭ የሆኑ አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር 3ኛ ዙር ውክልና የመወጣት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂደዋል። በመድረኩ ወረዳው በ2017 ዓ.ም ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስራዎች የሚዳስስ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። በዚህም በውይይት መድረኩ ነዋሪዎቹ በወረዳው አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለፅ የወጣቶች የስራ…
/የኛ ቁጠባ እና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር 3ተኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ
በመርሃ-ግብሩም የ2017 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም እና የኦዲት ሪፖርቶች እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ፀድቋል። በመድረኩ የተገኙት በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮምሽን የፋይናንስ ህብረት ስራ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ዱፌራ የኛ ቁጠባ እና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም አሁን ላይ እያከናወናቸው የሚገኙት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረው፤ በሁለት…
የድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017ዓም የስራ አፈጻጸምና የ2018 እቅድ ትግበራ ሰነድ ከፈጻሚ አካላት ጋር ተፈራረመ
የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችን በቀጣይ በጀበት አስቀጥሎ ለመጓዝ እና የቀሩ ውስንነት የታየባቸው ተግባራትን ቆጥሮ በመለየት የተሻለ ስኬት ማስመዝገብ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ መሆኑን ያነሱት የወረዳ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ምስራቅ፣ የፓርቲና የመንግስት እቅዶችን በጋራ ገምግመን የተግባባኔባቸውን ነጥቦች በቃልኪዳን ሰነድ ማስፈር ያስፈለገው የሚታይ ውጤት ለማስመዝገብና ተጠያቂነትን ለማስፈን ነው ብለዋል ። የወረዳው ካቢኔ አባላትና የዘርፍ ፈጻሚዎች…
ለአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ
“ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞ እንዲሁም የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች ላለፍት አራት ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል ። በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ቃል በተግባር የተገለጠበት የፓርቲው ያለፉት ዓመታት ጉዞ እንዲሁም በቀጣይ ስኬቶችን ለማስቀጠል…
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሚኤሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን አስጀመሩ
የሚኤሶ ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ሁለት ክልሎችን እና የድሬዳዋ ከተማን እንደሚያስተሳስር የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሎች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መስተጋብር የማጎልበት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ከወደብ ወደ ማዕከላዊ የሀገራችን ክፍል የሚደረጉ…


