በትንሿ ኢትዮጵያ፣ በበረሀዋ ገነት፣ በጉራማይሌዋ የፍቅር ከተማ ድሬ ገብተናል፡፡
በድሬዳዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ በቆይታችን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የስራ ሂደት የምንመለከት ይሆናል፡፡


