ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዝዳንቶች ጋር መከሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ ከ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክትባት ጥምረት (ጋቪ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳኒያ ንሽታር (ዶ/ር) ጋርም ምክክር አድርገዋል፡፡ EBC

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሱሉሁ ሳሚያ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንቶቹ ጋር በቀጣናዊ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ EBC

Read More

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች ነው -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ…

Read More

ሃመታ ሁንዳ የተሰኝ በገጣሚ አብዲ አህመድ የተፃፈ የግጥም ሰብብስብ የያዘ መፀሃፍ ለምርቃት በቃ

የሰው ልጅ በህይወት እስካለ የሚኖርበትን ማህበረሰብ ያየውን የማረውንና የተገነዘበውን እውቀት ፅፎ አሁን ላለውም ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት እንዳለበት እሱም በራሱ እይታ አጠቃላይ እይታ ካስተዋለውና ካደገበት ማህበረሰብ ነባራዊ እውነታ የተመሰረተ ስራዎችን በማቀናጀት ለህትመት እንዲበቃ ማድረጉን የመፀሃፉ ደራሲ ወጣት አብዲ አህመድ በምረቃ ስነ-ስረአቱ ላይ ገላጿል። በመፀሃፉ ዝግጅትና ህትመት በርካታ አካላት ድጋፍ እንዳደረጉለት የገፀው ደራሲው የኪነጥበቡ ዘርፍ…

Read More

በአስተዳደሩ በከተማ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ በአረንጓዴ ልማት ላይ ተሰማርተዉ ለሚገኙ ወጣቶች እና ለከተማ ወረዳ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ ተሰጠ።

የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በSUNCASA ማቺንግ ፈንድ ፕሮጀክት ለከተማ ወረዳ አመራሮች እና በአረንጓዴ ልማት ላይ ተሰማርዉ ለሚገኙ ወጣቶች በከተማ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ግንባታ (Green Infrastructure Development) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ አካሂዷል። የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ፣ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ቡድን መሪ እና የSUNCASA ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ደረጀ አቢቲ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በሁለት ዋነኛ…

Read More

የብልጽግና ፓርቲ ከቃል እስከ ባህል ብሄራዊ ትርክት ዙሪያ የዋሂል ክላስተር ኮሪሶ ወረዳ የፓርቲው አባላት ውይይት አካሄዱ።

በዉይይቱ ህብረ ብሄራዊ መግባባትን በሃሳብ አንድነት ለማጠናከር ብሄራዊ ትርክቶችን ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀመጡ የፓርቲው አቅጣጫዎች ላይ ገንቢ ሃሳቦች ተንሸራሽረዋል። በግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር የተመዘገበው ወቅትን ያላማከለ ውጤታማነት በጥሩ አፈጻጸም በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን በድሬደዋም ለግብርና ምቹ ባልሆነ አየር ንብረት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉ በተለያየ ጊዜ መነሳቱም የዋሂል ክላስተር…

Read More

የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ አዲስ አበባ ገቡ

የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ ለ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለፕሬዝዳንቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል። EBC

Read More

የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮ አዲስ አበባ ገቡ

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮ አዲስ አበባ ገብተዋል። ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። EBC

Read More

የጥቁሮች ታሪክ ወር” እና የሥርዓታዊ ጭቆና ሰለባ ሆነው የቀጠሉት ጥቁሮች

እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ሮዛ ፓርክ እና ማልኮም ኤክስ ያሉ የሰብአዊ መብት መሪዎች ይታወሱበታል። እንደ ጆርጅ ዋሽንግተን ካርቨር፣ ማዳም ሲ ጄ ዎከር እና ጋሬት ሞርጋን ያሉ ጥቁር የፈጠራ ሰዎች ዛሬም ታሪካቸው ይነገርበታል። እንደ ማያ አንጄሉ፣ ጀምስ ባልድዊን፣ ቶኒ ማሪሰን ያሉ የጥቁር ባህል አቀንቃኝ ጥበበኞች ደግሞ ይወደሱበታል። እንዲሁም እንደነ ባራክ ኦባማ፣ ካማላ ሃሪስ እና ኔልሰን ማንዴላ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመከላከያ ሠራዊት ጀነራል አመራሮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመከላከያ ሠራዊት ጀነራል አመራሮች ጋር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ “ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከመከላከያ ሠራዊታችን ጀነራል አመራሮች ጋር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።” ብለዋል፡፡

Read More