ወጣቱ ራሱን በመረጃ በማብቃት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የበኩሉን አይነተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
“በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የበቃ ዲጂታል ድሬዳዋን እውን የሚያደርግ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ወጣት ክንፍ ፅህፈት ቤት በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣት ክንፍ አመራሮች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ፡፡ ወጣቱ መንግስት የሚያከናውናቸውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዴፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን በንቃት በመከታተል ራሱን በመረጃ በማብቃት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የበኩሉን አይነተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ…


