በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የግል ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለኢፌድሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የብርና የአይነት ድጋፎችን አደረጉ፡፡
በጁንታው ቡድን በህግ ማስከበርና የሀገር ህልውና በማስጠበቅ ላይ ሆነው ለተሰዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች በርክክብ ስነ ስርዐቱ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡ በስነ ስርአቱ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የአስተዳደሩ ፖሊስ ከሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም የአስተዳደሩ ካቢኔ አባት ተገኝተዋል፡፡ በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስርአቱ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀሀር እንደተናገሩት የሀገራችን መከላከያ ስራዊት በትግራይ ክልል የመሸጉትን የህወሃት…


