የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ትኩረት በመስጠት የተሻለች ኢትዮጵያ መፍጠር በሚቻልበት መንገድ ሁሉም ሊረባረብበት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆጃቸው ያጡ ህፃናት ማህበረሰቡ ሊደግፋቸው ይገባል ሲሉ የድሬ ዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ሠራተኞች ለህጻናቱ ማሳደግያ ማዕከል እና ለትምህርት ቢሮ የትምህርት መርጃ መሳሪያና ለህጻናቱ ደግሞ የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳ ቁስ ድጋፍ አበረከቱ፡፡ በድጋፍ መስጠት ስነ-ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ እንዳሉት የሀገር ግንባታ ከታች ይጀምራል እነኝህ…


