ከመብራት አገልግሎት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም የከተማዋ ነዋሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩትን ጥያቄዎች ከመፍታት አኳያ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ ።
በከተማችን ድሬዳዋ ከመብራት አገልግሎት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ነዋሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩትን የተለያዩ ጥያቄዎችን ከመፍታት አኳያ የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰራቸውን ስራዎች አስመልክቶ የተቋሙ ሀላፊ የሆኑት አቶ ፍቅረማርያም አለማየሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ። በተለይም ከአስቸኳይ ጥገና ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰራር በመቀየር በዘመናዊ መንገድ አገልግሎቱን በመስጥትና በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ የደንበኞችን ቅሬታ ከመፈታቱም በዘለለ ከዚህ…


