በድሬዳዋ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዳዳ ገጠር ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የድህረ ተከላ እና የደን እንክብካቤ ስራ ተካሄደ።
#DGC ህዳር 28/2017 የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዳዳ ገጠር ቀበሌ ላይ መምህራን ፣ ተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ያሳተፈ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ድህረ እንክብካቤ ስራዎችን አከናወኑ። የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማት ቡድን መሪ አቶ ማሙሽ ዘውዱ በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት እንደገለፁት ችግኞችን ከተከሉ በኋላ በመኮትኮት ፣ ውሃ…


