የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ ስራ አስኪያጅን የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ ስራ አስኪያጅን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዛሬው እለት የገመገመ ሲሆን በተካሄደው የመስክ ምልከታ የተሰሩ ስራዎችን መነሻ በማድረግ የከተማ ስራ አስኪያጅንና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡ በዛሬው የውይይት ግምገማ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ የቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂምን…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) አሰራር ስርዓትን ለመተግበር ከፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ::

በዚህም የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የዲጂታል የኢትዮጲያን ጉዞ ለማፋጠን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) አሰራር ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል። በኤሌክትሮኒክስ ግዢን መፈፀም ብልሹ አሰራርን በመቀነስ ወጪና ጊዜን እንደሚቆጥብ የጠቆሙት ም/ከንቲባ ሀርቢ የአሰራር ስርዓቱን አስተዳደሩ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኑን አመላክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር በስፋት ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝና “በመሶብ ድሬ”…

Read More

“በወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል” – የወረዳ 09 ነዋሪዎች

በድሬዳዋ ወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ አያይዘውም ከኮሪደር ልማቱ በፊት በአካባቢው በስፋት ያረጁ፣ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች ይገኙ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት ግን ያረጁ ቤቶች ውበት ባላው እና በዘመናዊ መልኩ በአዲስ ተሻሽለው እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ለአካባቢ…

Read More

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና የመውጫ ውይይት አካሄደ።

የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአካል በመገኘት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ለመገምገም በተዘጋጀው ቼክ ሊስት እና እየካሄደ ባለው የመስክ ምልከታ የተሰሩ ስራዎችን መነሻ በማድረግ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ፣ የቢሮ እና የገቢዎች ባለስጣን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የበጀት የኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከማኔጅመንት…

Read More

የ2018 ዓ/ም የጥምቀት በአል ፍጹም ሰላማዊ ከመሆኑም ባሻገር በከተማችን ድሬዳዋ ይበልጥ መተሳሰብ እና ፍቅር ጎልቶ የታየበት ነው :-ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ

በአማረ ሃይማኖታዊ ስርዓት የተከበረው የጥምቀት በአል ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለምንም የትራፊክ አደጋ ተከብሮ እንዲያልፍ በማድረግ ረገድ የድሬዳዋ ፖሊስ ሌሎች የፀጥታ አካላት እና አጋዥ የማህበረሰብ ክፍሎች ላደረጉት የላቀ አስተዋጾኦ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ከበአሉ አስቀድሞ እቅድ በማውጣትና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማወያየት…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ሰራ አስኪያጅ እና ተጠሪ ተቋማቱ ላይ የመስክ ምልከታውን አደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት የከተማ ስራ አስኪያጅ ተጠሪ ተቋማት በሆኑ የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ፣ የቄራ አገልግሎት ድርጅትንና መንገዶች ባለስልጣን ላይ የንብረት ማስቀመጫ መጋዘኖችን (እስቶሮች) ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ በተከበሩ ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ ሰብሳቢነት የሚመራው የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ስራ አስኪያጅ እና ተጠሪ ተቋማት በሆኑት የፅዳትና…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት አንድም የመገለጥ፣ ሁለትም የእርቅና ዳግም የመወለድ ምልክት ነው፡፡ በቀደመው ዘመን አዳምና ሔዋን በፈጸሙት ሐጥያት የሰው ልጅ ከአምላኩ ተቀያይሞ የፍዳ ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ዳሩ ግን ሰው በሐጥያቱ ልጅነቱን ቢነጠቅም እስከወዲያኛው ጠፍቶ አልቀረም፤ አባቱን ያስከፋ ሥህተት ቢሰራም እስከመጨረሻው ተረግሞ አልኖረም፡፡ አጥቶ የነበረውን የልጅነት ጸጋ በክርስቶስ ዳግም ተቀብሏልና፡፡ ክርስቶስ…

Read More

የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::

የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ዛሬ ጠዋት በመረቅነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ይኽን በግልጽ ተመልክተናል ሲሉ አክለዋል። ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃልም ብለዋል። ኢትዮጵያ ሀገራችን በባሕል፣ በተፈጥሮ እና ታሪካዊ ጥሪቶች የታደለች በመሆኗ፤ ዛሬ ያለንን ጉልበት…

Read More

ከንቲባ ከድር ጁሀር የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የከተራ እና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፥ “ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ብለዋል። ከንቲባ ከድር በመልዕክታቸው፥ የጥምቀት በዓል በቅርስነቱ በዩኔስኮ በመመዝገቡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴት ነው ብለዋል። የከተራና ጥምቀት በዓል የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ሁነት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከብር የድሬዳዋ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል::

አቶ ብሩክ በመቀጠል እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ከአሉ በኋላ አያይዘው … በዓለ ጥምቀቱ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከሃይማኖታዊ ክብረ በዓልነቱ በዘለለ ማኅበራዊ ኑሯችን የሚደምቅበት፣ በልዩ ልዩ አልባሳት የምናጌጥበት፣ ልዩ ልዩ ኅብረ ዜማዎችን የምንሰማበት ባህላዊ እሴቶቻችን የሚስተናገዱበት በዓል ጭምር ነው ብለዋል። እንደ ጥምቀት ያሉ የአደባባይ በዓሎቻችንን በአማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሁላችንም እኩል ልንደክም ይገባል ብለዋል።…

Read More