ተቋማት ሰው ተኮር የሆነ አግልግሎት በመስጠት ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ተጠቆመ

በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት አንፃር ከተገልጋዮቻቸው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችላቸው መሰው ተኮር አገልግሎት እቅድ በማዘጋጀት እንዲተገብሩ በመደረግ ላይ ሲሆን ከብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተውጣጡ የሱፐርቪዥን ቡድኖች የተቋማትን የ2017 በጀት አመት የ3ኛው ሩብ አመት የሰው ተኮር አገልግሎት እቅድ…

Read More

በአፍሪካ እና በሌሎች የአለም አገራት ከሚገኙ እህት ከተሞች ጋር ወዳጅነት በመፍጠር፥ ለድሬ ሁለንተናዊ እድገት መፋጠን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ቀጥለናል።

በማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ከንቲባ ሃሪላላ ራማንትሶአ የተመራ ልዑክ ቡድን፥ ለሁለት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ያደረገው ጉብኝት እና ውይይት የዚህ ጥረታችን አንዱ አካል ነው። ክብርት ከንቲባዋ እና ልዑካቸውን እንዲሁም የ’ትንሿ ኢትዮጵያ’ ድሬ አምባሳደር የሆነችው ውድ እህቴ ገነት ወ/ስላሴን ከልብ እያመሰገንኩኝ፥ በቀጣይ ከማዳጋስካሯ አንታናናሪቮ ከተማ ጋር በተለያዩ የልማት ዘርፎች በትብብር ለመሥራት፥ አስተዳደራችን ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ።

Read More

የታዳሽ ሀይል ቴክኖሎጂ ለዜጎች ስራ መፍጠሪያ ብሎም ሀብት ማፍሪያ መሆን የሚችል ዘርፍ መሆኑ ተገለፀ

የድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከየአርዳ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በዘርፉ ትምህርትና ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልፆዋል። ADRA ፕሮጀክት የ5000 ዋት solar PV system installation and commissioning ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በአስተዳደሩ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥርት ወጣቶችን ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ይገኛሉ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በኢንደስትሪውና በማኒፋክቸሪንጉ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ

ማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ከንቲባ ሀራላላ ራማናቶሳ የተመራው ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ እያከናወነ የሚገኘው ጉብኝት ቀጥሎ ልኡክ ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም በመስተዳደሩ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጠና፣ ደረቅ ወደብን፣አዲሱ ምድር ባቡርን እንዲሁም ሀሴት የህክምና መገልገያ እቃዎች ማምረቻን በመመልከት ልኡኩ በቬራ ፖስታ መንገድ በኮሪደር…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በድሬዳዋ የገበያ ማእከላት ተወካዮችና የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች ጋር የኢትዮጵያ ብሐቤራዊ መታወቂያ “ፋይዳ”ተመዝግበው በመያዝ ዲጅታል መታወቂያው የሚያስገኛቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እንዲያገኙ ለማስቻል ባዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ላይ ተወያይተዋል

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ለየት ባለ ሁኔታ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ግንባር ቀደም የሚያደርጋትን ስራ በማከናወን ላይ መሆኗን ጠቅሰው ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ዲጂታል መታወቂያውን ከሚያዚያ እስከ ሰኔ 2017 ዓ/ም ድረስ አስተዳደሩ በሚያዘጋጃቸው የመመዝገቢያ ማእከላት ተመዝግበው ሙሉ ለሙሉ መታወቂያውን መያዝ የሚያስችል ንቅናቄ መጀመሩን…

Read More

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በመረዳት ሁሉም ማህበረሰብ እንዲመዘገብ ጥሪ ቀረበ

በድሬዳዋ አስተዳደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በየተቋማት እየተካሄደ ሲገኝ፤ በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ፈት ቤት ምዝገባው ተጀምሯል፡፡ በዚህም ምዝገባውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱለዚዝ ሻፊ የዲጂታል መታወቂያ ህዝባዊ አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ የዜጎችን የጤና እና የትምህርት ደረጃ መረጃ በማገናዘብ ፎርጅድ እና አጠቃላይ ህገ ወጥነትን ለመከላከል ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ተወያዩ።

<<የመሃሉ ዘመን!>>በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር የሴክተር እና ወረዳ አመራሮችና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የተወያዩ ሲሆን የውይይቱ ዋንኛ አላማም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ተከታታይ 7 አመታት ለውጡን ለማፅናት በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ውስጣዊ፣ ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከት ሰራተኞችና አመራሮች የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በቀጣይም እንደሀገር ሊገጥሙ…

Read More

“የነገዋን ድሬዳዋ ለመገንባት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ትልቅ ምስጋናዬን አቀርባለሁ “፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር

” የድሬዳዋ ፖሊስ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም እንዲሆን ሚናችሁ ከፍተኛው ነበር “፡- የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዣዥ ክቡር ኮምሽነር አለሙ መግራ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የስራ ጊዜያቸው ላጠናቀቁት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚዎች የምስጋናና የክብር ሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ ፡፡ በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል። ለዚህም ማሳያ የሆነውን የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከል ዛሬ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ይኽን አዲስ ማዕከል የሚገልጡ ሶስት ቁልፍ…

Read More

የልማት ድርጅቶችን በአዲስ አስተሳሰብና መንገድ መልሶ በማደራጀት ለመምራት በመቻሉ እመርታዊ ለውጥ መጥቷል፡- የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

የንግድ ባንኮች ባለፉት ስምንት ወራት ከሰጡት 473.9 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 76.6 በመቶ የሚደርሰው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል። ይህም የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ተገቢውን ሚና እንዲጫወት የተቀመጠው ፖሊሲ በተግባር እየተገለጠ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብሏል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫው። የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር…

Read More