የዝቅተኛ ነዋሪ ዜጎችን ጫና ለማቃለል የ212.2 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተደርጓል፦ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
በተያዘው ዓመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት የ8.4 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ እና በየዘርፉ ደግሞ ግብርና በ6.1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ በ12.8 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን በ12.3 በመቶ እና አገልግሎት በ7.1 በመቶ እንደሚያድጉ ተገምግሟል። የ9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ ሲያሳይ፤ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ያለው ድርሻም ወደ 13.7…


