“በመጪው የረመዳን ወር ጾም ህዝበ ሙስሊሙ አቅመ ደካሞችን በመርዳት በጎ ተግባራትን በማከናወን ሊያከበር ይገባል” የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር
የ1446ኛው የረመዳን ወር ፆም ከ6ቀናቶች በኃላ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ 30ኛው የምርኩዝ መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ መሻኢኾች ፣ኢማሞች፣ኡስታዞች በተገኙበት በተለያዩ የእስልምና ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል። በመርሀ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካይ ኡስታዝ አብደላ በንግግራቸው የምርኩዝ መድረክ ወደ ድሬዳዋ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ ለ1446 ዓ.ሂ የረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ…


