የአንካራው ስምምነት ለቀጠናው ሰላም ትልቅ እፎይታ ነው – የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪው::

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ያደረጉት ስምምነት ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር ለሌሎች የቀጠናው ሀገራት እና ለቀጠናው ሰላም ትልቅ እፎይታ ነው ሲሉ የአፍሪካ ጉዳዮች ተማራማሪ አቶ ሙሉጌታ ከተማ ይፍሩ ገለፁ፡፡ ተመራማሪው ከኢቢሲ ዶትስትሪም ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የስምምነት ዜናው ግጭቱን ለራሳቸው ተጠቃሚነት ለማዋል ያሰቡ ሀገራትን እና በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን ከዓላማቸው የሚያደናቅፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስምምነቱ ውጤታማ እንዲሆንም ያሉ ችግሮችን እየነቀሱ…

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን ነገ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል::

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል። በስብሰባው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል። ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።…

Read More

በአስተዳደሩ ላይ የሚገኙ የህንፃ ግንባታ ስፍራዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መታጠር እንዳለባቸው ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ውስጥ በአስተዳደሩ የንግድ ቤቶች ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ ቢልቦርድና መሰል በህንፃዎች ላይ ተለጣፊና ተንጠልጣይ ማስታወቂያዎችን ፍቃድ መስጠት ማደስና አመታዊ እድሳት የሚያደርጉ ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን በአስተዳደሩ ላይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ሳጥኖች እና ቢልቦርዶች ፍቃድ ከማውጣት አንስቶ…

Read More

በኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የተመራ ልዑክ የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩትን የሁለተኛው ምዕራፍ የግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም ጎበኘ::

ከሰሞኑ በኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የተመራ ልዑክ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ ሱፐርቪዥን በማድረግ ላይ ሲሆን በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ…

Read More

“ሄር ኢሴ” ግጭት አፈታት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ከመቻሉም በላይ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ለዘመናት ተቻችሎና አብሮ በመኖሩ ለዘመናዊ ፍርድ ሂደትም የራሱ የሆነ የጎላ ሚና እንዳለው ተገለፀ::

በ19ኛው የዩኒስኮ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ “ሄር ኢሴ” የሶማሌ ኢሣ ማህበረሰብ ያልተጻፈ ባሕላዊ ሕግ በሰው ልጆች ወካይ ዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት ያስመዘገበው ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ጠዋት ወደ ድሬዳዋ መግባቱን ተከትሎ በኡጋዝ ሙስጠፌ መሀመድ ቤት ደማቅ የአቀባበል መርሀ ግብር ተከናውኖለታል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት…

Read More

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን የተመራውና በፓራጓይ ርዕሰ ከተማ በተዘጋጀው 19ኛው የዩኒስኮ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ “ሄር ኢሴ” የሶማሌ ኢሣ ማህበረሰብ ያልተጻፈ ባሕላዊ ሕግ በሰው ልጆች ወካይ ዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት ያስመዘገበው ልዑካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገባ።

ልዑክ ቡድኑ በዛሬው እለት ጠዋት ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስም በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና በመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። “ሄር ኢሴ” ያልተጻፈ ባህላዊ ህግ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ አባላት በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። ሄር ኢሴ” ባህላዊ መተዳደሪያ ህግ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን…

Read More

የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በወረዳ 9 አስተዳደር ስር እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ቱሩፋት እንዲሁም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን ጎበኙ

በዚህም የወረዳ 9 አስተዳደር በ 5 ወራቶች ውስጥ በአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንዲሁም በሌማት ቱሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ለእንግዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን፤ በመስክም በልብስ ሽያጭ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶችን በተጨማሪም በሌማት ቱሩፋት ስራም የማር ምርትን እንግዶች ተመልክተዋል። እንግዶች ቀጥለውም የከተማ ስራ አስኪያጅ G+5 የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክትን…

Read More

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በባቡር ዘርፍ በምስራቅ አፍሪካ የልቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ

የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ሲገኙ፤ በከሰዓቱ መርሀ ግብርም እንግዶቹ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ጎብኝተዋል። በዚህም በኢስት አፍሪካ እስኪልስ ፎር ትራንስፎርሜሽን ኤንድ ሪጅናል ኢንተርግሬሽን ፕሮጀክት 14 ሚልየን 850 ሺ ዶላር ተበጅቶለት እየተተገበረ የሚገኘውን ፕሮጀክት…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ በርካታ ወጣቶች የስራ ባለቤት መሆናቸው ተገለፀ::

በዛሬው እለት የኢፌድሪ ማዕድን ሚንስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ ወረዳ ሁለትና ሶስት አስተዳደር በውበት ሳሎን ስራ፣ በእንጨት ስራ ውጤቶች እንዲሁም በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። እንዲሁም ደግሞ በወረዳ 3 አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በልማት፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደር፣…

Read More

በዓለም ቅርሶች መዝገብ የተመዘገበውን የሔር ኢሴን ቅርስ የማስተዋወቅ ስራዎች እንደሚሰራ ተገለፀ

ሀገራችን ኢትዮጲያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) በዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ የተካተቱ በርካታ የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ያሏት ሲሆን አሁን ደግሞ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆነ የማይዳሰስ ቅርስ ነው የተባለው የሱማሌ-ኢሳ ማህበረሰብ የቃል ልማዳዊ ሕግ ( ሔር ኢሴ ) በ 19 ነኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) ጉባኤ በማይዳሰሱ…

Read More