በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም እንደአስተዳደር የአርሶአደሩን ህይወት ከማሻሻል ባሻገር ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን ማረጋገጥ መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናገሩ።
ከተለያዩ ክልል ግብርና ቢሮ የተወጣጡ ባለሞያዎችና የዘርፉ አመራሮች በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ላይ አመታዊ ግምገማና ስልጠና ተጀምሯል። የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ፣የአለም ባንክ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራምና የክልል ስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በአስተዳደሩ በግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የምግብ ሥርዓት…


