የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በመረዳት ሁሉም ማህበረሰብ እንዲመዘገብ ጥሪ ቀረበ
በድሬዳዋ አስተዳደር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በየተቋማት እየተካሄደ ሲገኝ፤ በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ፈት ቤት ምዝገባው ተጀምሯል፡፡ በዚህም ምዝገባውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱለዚዝ ሻፊ የዲጂታል መታወቂያ ህዝባዊ አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ የዜጎችን የጤና እና የትምህርት ደረጃ መረጃ በማገናዘብ ፎርጅድ እና አጠቃላይ ህገ ወጥነትን ለመከላከል ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን…


