በመሰረታዊ የሸቀጥ ምርቶች ላይ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ሸማች ማህበራት ላይ የዋጋ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ-ሀይል በማቋቋም እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱሰትሪና ኢንቨሰትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀር አስታወቁ፡፡
ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ፣ ከብልፅግና ፓርቲ ፣ከፌደራል አቃቢ ህግ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ፣ ከዘጠኙ የከተማ ቀበሌዎች ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርገዋል። ምክትል ከንቲባው በከተማው የመሰረታዊ ፍላጎት እቃዎች ላይ ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ዋጋ በሚጨምሩ ፣ምርት በሚያሸሹና በሚያከማቹ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና የሸማች ማህበራት ላይ የተጀመረው አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ…


