በድሬዳዋ “ለፍቅር እሮጣለሁ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው በድሬደዋ በርካታ አላማዎች ያነገበ “ለፍቅር እሮጣለሁ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።
ውድድሩ የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ከሚመራው ሂማ ሬስ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በሺዎች የሚገመቱ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እና የአገራችን ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበትን የ10ሺ እና የ5ሺ ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ታዋቂዋ አትሌት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ፣ የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊራንኦል ቡልቻ ሌሎች በርካታ እንግዶች ናቸው።…


