ከብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣
ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ሀገራዊ የደኅንነት ሁኔታ የገመገመ ሲሆን፣ በቀደሙት ወራት ተለይተው የነበሩ ሀገራዊ ሥጋቶችን መሠረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትንና ያጋጠሙ ውስንነቶችን ለግምገማው መነሻ አድርጓል። የደኅንነት ምክር ቤቱ ሰኔ 1 ባካሄደው ስብሰባው ወቅት በአስቸኳይ ለማከናወን ተወስነው ከነበሩ ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- 1. አሸባሪና የታጠቁ ቡድኖችን በአመራራቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ለመደምሰስ፣ 2. ለጠላት ዐቅም…


