በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጠው የሲቲስካን ማሽን፤ ከችግር እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ገለፁ፡፡
ከዚህ ቀደም በመንግስት ሆስፒታል አገልግሎቱ ባለመኖሩ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ መንገላታት ይገጥማቸው እንደነበር የተናገሩት ተገልጋዮቹ፤ አቅማቸውን ያላገናዘበ ክፍያ ይጠየቁ እንደነበርም አስታውሰዋል። ተገልጋዮቹ አክለውም በቅርቡ በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ስራ የጀመረው የሲቲ ስካን ማሽን፤ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ለማግኘት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት እና የተጋነነ የገንዘብ ክፍያ እንዳስቀረላቸው ገልፀው፤ በዚህም መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ…


