ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሪፈራል ሆስፒታሉን ሙሉ ለሙሉ ተረከበ
ሆስፒታሉ በአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ በተደረገላቸው አካላት ተጎብኝቷል:: በግንባታው መዘግየት በርካታ አመታትን ያስቆጠረው የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል የአስተዳደሩ ካቢኔ በጥር 15 ቀን 2010 ዓ/ም ተወያይቶ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሙሉ ለሙሉ አሁን ባለበት ሁኔታ ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በከንቲባ ፅ/ቤት በተደረገው የሪፈራል ሆስፒታሉ ርክክብ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል…


