ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል በየዓመቱ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የምታስቀርበት ፋብሪካ
ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል ግዢ በየዓመቱ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የምታስቀርበት ግዙፉ የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል። የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የገጸ ምድር እና የከርሰ ምድር የማዕድን ሀብቷን አልምታ እና እሴት ጨምራ በመጠቀም በኩል ለረጅም ዓመታት…


