በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ::
ቢሮው በ100 ቀናት እቅድ ውስጥ ከፍትህ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ነጻ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተግባራዊ ማድረጉን የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሌሊሴ አህመድ ገለፁ ። ሴቶች ህጻናት ያለምንም የጥቃት ስጋት እና የተጠናከረ የመረጃ ድጋፍ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማስቻል…


