ሀብቶቻችንን ወደ ትክክለኛ የቅድሚያ ትኩረት ካዋልን ማኅበረሰቡን ማሻገር እንደምንችል ማመን ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ረቡዕ በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የነበረንን የሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነሥርዓት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። እነኚህ ባለሶስት መኝታ ቤት መኖሪያዎች፤ ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ሲሆን፤ በተመጣጣኝ አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች…


