በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል ተባለ::
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት÷ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ባለሃብቶች እና ባለድርሻ አካላት የትስስር ፎረም ለመመስረት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሐር በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ወሳኝ ከሚባሉት በተለይ ከሰው ሀይል÷ የማቴሪያል÷ከማምረቻና ከመሸጫ ቦታ ምችችትን ጨምሮ ከመብራትና ከብድር አቅርቦት እረገድ የተለያዩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ አስረድተዋል። ችግሩ በተለይም ጉዳዩ በሚመለከታቸው…


