የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴክተር፣ የወረዳና የክላስተር ህብረቶች የ2018 አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን በትላንትናው ዕለት በጀመረው ድጋፋዊ ክትትል የአስተዳደሩ ሴክተር፣ ወረዳና ክላስተሮች የብልፅግና ፓርቲ ህብረቶችን የ2018 የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በማካሄድ ላይ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ በህብረቶቹ የተከናወኑ የፓርቲ ስራዎችን የአፈፃፀም ደረጃ በመፈተሽ በትግበራ ምዕራፍ የተሻለ አፈፃፀምን ለማስመዝገብ ግብዓት የሚሆኑ ግብረ-መልሶች መስጠትን ዋነኛ ዓላማ አድርጎ በመካሄድ ላይ…


