በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

    6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ ነፃና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆንና ምርጫውን በበላይነት በማሸነፍም የህዝብ ተወካዮች መቀመጫ የማግኘት ግቡን እውን ለማድረግ በሚያግዝ መልኩ ዛሬ ለፓርቲው የታችኛው መዋቅር አመራርና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው ። በስልጠናውም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸው አቋሞች ፣ ባለፉት 3 አመታት ፓርቲው ያሳካቸው ድሎችና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሰነቀው ህልም ለአባላቱ በሰፊው ተገልጿል…

    Read More

      የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች አለም አቀፍ ማህበር” ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ::

      በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ በተካሄደው የድጋፍ መርሀግብር ላይ ወ/ሮ ሜላት ብርሀኔ ማህበሩን በመወከል ባደረጉት ንግግር በአሜሪካና በአውሮፓ በሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች የተመሰረተው ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል:: በዛሬው ድጋፍም ከተለያዩ የአስተዳደሩ የከተማ ቀበሌዎች ለተመረጡ 200 አቅመ ደካማ የእስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በዓል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 1ሺህ ብር…

      Read More

      እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር ረመዳን በዓል፥ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ።

      ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር። ዘንድሮ የረመዳን ወር እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾም በተመሳሳይ ቀን በመጀመራቸው ፥ ከጥንትም ‘በትንሿ ኢትዮጵያ’ #ድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ እሴት፥ በይበልጥ ደምቆ መታየቱ የማይካድ ሀቅ ነው። የነገዋ የኢድ ዕለት፥ በረመዳን የጾም…

      Read More

      በድሬዳዋ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው

      አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ይገኛል። በነገው ዕለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረትም በአስተዳደሩ የምርጫ ቁሳቁስ ከትናንት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ ያሲን…

      Read More

      የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፃቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተልምለፏል።

      በአዲስ አበባ ቆይታችን ፥ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ከተፈራረምነው የእህት ከተሞች ስምምነት ባሻገር ፥ ሰው ተኮር በሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት የአመራር ሰጪነት ሚናችንን ለማጎልበት የሚረዱ ግብዓቶችን አግኝተናል። የአስተዳደራችን ካቢኔ በቀጣይ፥ በስማርት ሲቲ፥ በተቋማት ሪፎርም ትግበራ እና ምገባ ፕሮግራም፥ እንዲሁም በካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙሪያ ያገኘውን ልምድና ተሞክሮ ወደ መሬት በማውረድ፥ ለድሬዳዋችን ሁለንተናዊ እድገት በይበልጥ እንደሚተጋ አምናለሁ።…

      Read More

      በዩኔስኮ የአለም የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ከተመዘገበ ሁለተኛ አመቱን የያዘው የሹዋል ኢድ በዓል በድሬዳዋ በድምቀት ተከበረ

      1446ተኛው ሒጅርያ ሹዋሊድ ክብረ በዓል “የአንድነት፣ የሰላም፣ የልማትና የብልፅግና ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ በድምቀት ተከብሯል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በሀረሪ ብሔረሰብ ልዩ ባህላዊ መገለጫ ለሆነው የሸዋል ዒድ ክብረ በአል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ከንቲባ ከድር አያይዘውም በዓሉ ሰላምን፣ ፍቅርንና መቻቻልን የሚያንጸባርቅ በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ለቀጣይ…

      Read More

        የሴቶች ቀን በአስተዳደሩ በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡

        በድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግና አመራር ሰጪነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰራ የአስተዳደሩ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ገለፀ በአለም አቀፍ ደረጃ 108 ጊዜ በሀገራችን ለ43 የሴቶች ቀን ተከብሯል “የላቀ  ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በሚል” መሪ ቃል ሴቶች ቀን በአስተዳደሩ ሲከበር የድሬዳዋ አስዳደር የሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንዳሉት በድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችን አመራር…

        Read More

        የ9 ወር የተቋማት እና የወረዳዋች የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ

        የአስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ2017 በጀት ዓመት የተቋማትና የከተማ ወረዳዎች የለወጥ ስራዎችና የመልካም አስተደደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬቶችና የወረዳዎች የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ማስተባበሪያዎች በተገኙበት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ የአስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር:የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ እና የከንቲባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በወረዳም ሆነ በሴክተር…

        Read More

        የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) አሰራር ስርዓትን ለመተግበር ከፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ::

        በዚህም የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የዲጂታል የኢትዮጲያን ጉዞ ለማፋጠን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) አሰራር ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል። በኤሌክትሮኒክስ ግዢን መፈፀም ብልሹ አሰራርን በመቀነስ ወጪና ጊዜን እንደሚቆጥብ የጠቆሙት ም/ከንቲባ ሀርቢ የአሰራር ስርዓቱን አስተዳደሩ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኑን አመላክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር በስፋት ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝና “በመሶብ ድሬ”…

        Read More