ስዊፍት ትራንስፖርት የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች መሰረታዊ የጥገናና የአነዳድ ሁኔታ ላይ እንዲሁም የመኪኖቹ አጠቃቀም እና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ስልጠና ሰጠ
በዚህም በስልጠና መድረኩ የተገኙት የስዊፍት ትራንስፖርት ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ አሸብር ስዊፍት ትራንስፖርት የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ በርካታ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ ለተጠቃሚዎች እያከፋፈለ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ስዊፍት ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን ከማቅረብ በተጨማሪ ተሽከርካሪዎቹ አዲስ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ስለመኪኖቹ አጠቃቀም፣ ስለ መሰረታዊ የጥገናና የአነዳድ ሁኔታ እንዲሁም ስለ ደህንነት አጠባበቅ ላይ በዛሬው ዕለት ለአሽከርካሪዎች፣ ለመንገድ ትራንስፖርት ተወካዮች እንዲሁም በአጠቃላይ ለባለድርሻ…


