በድሬዳዋ አስተዳደር የተከበረው የጥምቀት በአል ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ መከበሩ ተገለፀ ።

    በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በአል በድሬዳዋ አስተዳደርም ተከብሯል ። በተለይም በአሉ በድሬዳዋ አስተዳደር ሲከበር በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ከጥምቀት ከተራ በአል አንስቶ ታቦታቱ ከመንበራቸው ወተው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዝማሬና እልልታ ታጅቦ በጥምቀተ ባህር ካደሩ በኋላ በጥምቀት በአል ቀን ታቦታቱ ወደ ደብራቸው በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በእልልታና በዝማሬ አጅበው በሰላም አስገብተዋል ። ከዚሁ የበአል…

    Read More

    የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በጋራ በመሆን በቅድስት ማርያም ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን በመገኘት የዓብይ ፆምን ፆመው በስርዓተ ቅዳሴ ለተሳተፉ የእምነቱ ተከታዮች የታሸጉ ውሀዎች እና ጣፋጭ ምግቦችን የመስጠት መርሀ-ግብር በዛሬው እለት አካሄዱ

    በመርሀ ግብሩ ሲያስተባብሩ ያነጋገርናቸው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በአብሮነትና በመተሳሰብ የፆም ወቅቱን እያመሰገንን ነው በማለት የተናገሩ ሲሆን፤ የዛሬው ዝግጅት ዋነኛ አላማም በድሬደዋ ሁሉም ሀይማኖት በመከባበርና በመተሳሰብ እንደሚኖር ለማሳየት መሆኑን ጠቁመዋል። አብሮነትና ፍቅር በተግባር በሚገለፅባት ድሬዳዋ ዛሬም ብዙዎች በተምሳሌትነት ሊወስዱት የሚገባ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በቀጣይም እንደዚህ አይነት የመቻቻልና የአብሮነት እሴትን የሚያጠናክሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ…

    Read More

    የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል

    በምርጫው የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት አስታወቀ። ፓርቲዎች የፖሊሲ ሀሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጣሂር ሮብሌ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ በሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለተካ ፓርቲዎች የድርጅቱን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ተጠቅመው አማራጭ…

    Read More

      ዛሬ በድሬደዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የዘጠኝ ሰው ህይወት ማለፉን ተገለፀ::

      አደጋው ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ ሸመንተሪያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መከሰቱን የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዲቪን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ባንታለም ግርማ ተናግረዋል ። አክለውም ከጠዋት ሁለት ሰአት ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ሰዓታት ዝናብ ሲጥል መቆየቱን በዚህም ሳቢያ እርዝመቱ 50 ሜትር የሆነ የግንብ አጥር በሶስት ቤቶች ላይ ተደርምሶ ከቀኑ ስድስት ከሀያ…

      Read More

      Dadka deggan Dir Dhabe ayaa muujiyay diyaar-garow buuxa oo ay ugu jiraan ka qaybgalka doorashada guud ee 7aad, iyagoo si firfircoon u diiwaangelinaya codbixiyeyaashooda isla markaana qaadanaya kaararka codbixinta.

      Waxay sheegeen in doorashadu tahay mid go’aamineysa masiirka mustaqbalka dalka, isla markaana ay tahay fursad muhiim ah oo muwaadiniintu ku gudan karaan xuquuqdooda dastuuriga ah iyo tan dimuqraadiga ah. Sidaas darteed, waxay ku booriyeen muwaadin kasta oo gaaray da’da codbixinta inuu si sax ah uga faa’iideysto xaqiisa codbixineed. Sidoo kale, waxay ugu baaqeen dhammaan muwaadiniinta…

      Read More

      የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 11 ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአሁን ሰዓት እያካሄደ ይገኛል::

      በጉባኤውም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የምክር ቤቱ 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 11 ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የምክር ቤቱን 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 3 ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የአስተዳደሩ የአስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ 2018 ዓ.ም የ 6 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት…

      Read More

      እንኳን ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል አደረሳችሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

      ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል የአደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች ዐርበኞች በዓል አደረሳችሁ ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ዐርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበት እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው።…

      Read More

      የድሬ አዋርድ አሸናፊዎች !

      የድሬ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ተሸላሚ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር። የበጎ ሰው ዘርፍ :- አቶ ወስን ቢራቱ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ ሲሆኑ አቶ ዳዊት በቀለ እና አቶ ዋለልኝ መኮንን የምስጋና ተሸላሚ ሆነዋል።

      Read More