ለሚኒሚዲያ ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጠ በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አዘጋጅነት በሚኒሚዲያ አዘገጃጀትና በኮቪድ 19 የትግበራ መመሪያ ዙሪያ በአስተዳደራችን ለሚገኙ የሚኒሚዲያ ተጠሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ አካላትን ማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል እንዳለ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሚኒሚዲያዎች ለትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ቅርብ በመሆን መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ አይነተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡ ይህ አሁን የተዘጋጀው ስልጠና በሚኒሚዲያ አዘገጃጀትና ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው የትግበራ መመሪያ ዙሪያ የሚኒሚዲያ ተጠሪዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ መሆኑን አቶ ሚካኤል ገልፀዋል፡፡ የሚኒሚዲያዎችን አቅም ለመገንባት…


