ዓድዋ ተረት እንዳይመስልብን!
የዛሬ 128 ዓመት ዕለተ እሑድ በዓድዋ ተራሮች አናት የወጣች ፀሓይ ለዓለም ብርሃን ኾናለች፡፡ እነሆ ፀዳሏ እያበራ ከትውልድ ትውልድ በላቀ ድምቀት እየተዘከረም ይኖራል፡፡ ከብዙ ጥረትና ጥምረት በኋላ ኢትዮጵያውያን ያሳኩት የዓድዋ ድል የዓለምን የፖለቲካና ታሪክ ፈር የቀየረ ነው፡፡ ወቅቱ አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች አፍሪካውያንን በባርነት ተናጋሪ እቃ አድርገዉ ከመገበያየትና ጉልበታቸዉን ወደ አውሮፓ ወስዶ ከመበዝበዝ ቀያቸዉን ተቆጣጥሮ የጥቍሮችን የተፈጥሮ…


