ህይወታቸውን መቀየር እንዲችሉ የተመቻቸውን የሙያ ስልጠና የወሰዱ ጎልማሳ የጎዳና ተዳዳሪዎች በዛሬው ዕለት ተመረቁ::
በአስተዳደሩ በጎዳና ላይ ኑሮዋቸውን ይመሩ የነበሩ ጎልማሶች በስደስት የተለያዩ የሙያ መስኮች ለአምስት ወራት ስልጠና ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡ ስልጠናው የድሬዳዋ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ከሀረርጌ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ጎዳና ላይ ይኖሩ የነበሩ አካላትን በመመልመል የተለያዩ ሙያዊ ስልጠና እንዲያገኙ በማመቻቸት የእራሳቸውን ህይወት የሚለውጡበት ሁኔታ ዓላማ ያደረገ መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ…


