“መልካጀብዱ ከአቧራና ከቁሻሻ ተላቆ ውበትን እየተጎናፀፈ ይገኛል” – የወረዳ 01 ነዋሪዎች::
በድሬዳዋ በወረዳ 01 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ አካባቢውን ከአቧራና ከቁሻሻ አላቆ አዲስ ውበትንና ገፅታን እያጎናፀፈው እንደሚገኝ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ። በዚህም የወረዳው ነዋሪ የሆኑት አቶ ነብዩ ደመቀ ከዚህ ቀደም የመልካ ጀብዱ መንገድ የተዘጋጋ በቁሻሻና በአቧራ የተሞላ እንደነበረ አስታውሰው፤ በአሁን ሰዓት በኮሪደር ልማቱ መንገዶች ተከፍተው ባማረ መልኩ እየተሰሩ እንደሚገኙና ይህም ለወረዳው አዲስና ማራኪ ገፅታን እያላበሰው እንደሚገኝ…


