የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋን የኮሪደር ልማት የፕላን ንድፍ ላይ ከኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስተር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በተገኙበት ውይይት አደረጉ።
በአሁኑ ሰአት በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት በመገኘት በወረዳው በ6 ወራት የተሰሩ የልማትና የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርትን እያደመጡ ይገኛሉ። በዚህም በሪፖርቱ በስራ እድል ፈጠራ፣ በንግድ ዘርፍ፣ ዲጂታል ድሬን በማፋጠኑ ረገድ፣ በወረዳ ደረጃ ገቢን በመጨመር እንዲሁም በሌማት ቱሩፋት ማለትም በእንቁላል፣ በማርና በወተት ምርት እንዲሁም በከተማ ግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል። በአጠቃላይ ከመድረኩ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ…


