በሰላምና ፀጥታ መደፍረስ ዋንኛ ተጠቂዎች ሴቶች በመሆናቸው በመላከል ረገድም ቀዳሚ ድርሻ እንዳላቸው ተገለፀ፡፡
የድሬዳዋ ኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ “አንድነትና ብልፅግና ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል ህዳር 21 እና 22 ተካሂዷል፡፡ ሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብደላ አህመድ እንደተናገሩት የኢህአዴግ እንቅስቃሴ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለአስተዳደሩ ሆነ ለመላው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና…


