የ16ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ አገር አቀፍ የወጣቶች ሲምፖዚየም <<ወጣትነቴን ለሀገሬ >>በሚል መሪ ቃል በዓሉ በሚከበርባት ድሬደዋ ተካሄደ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር በሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገር ወዳድነት እና በባለቤትነት ስሜት በመነሳሳት በኢትዮጵያ ሰላም፣እድገትና ብልፅግና እንዲሁም አንድነት አብሮነት ላይ ከእስከዛሬው የተሻለ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱና የዜግነት ግዴታችንን እንድትወጡ ሲሉ ለወጣቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በ16ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው አገር አቀፍ የወጣቶች ሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ…


