የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት በምክር ቤቱ አዋጅ ቁጥር 1/2000 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡- የጽ/ቤቱ አፈ-ጉባኤ በሚሰጠው አመራር መሰረት፡- ለምክር ቤቱና ምክር ቤቱ ለሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎች ውስጣዊ አካላት አጠቃላይ አስተዳደራዊ ግልጋሎት ይሰጣል፣ ለምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የሚያስፈልጉትን የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ያደራጃል የዘጋጃል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ የምክር ቤቱን ቃለ-ጉባኤዎች፣ ውሳኔዎችና ሰነዶች በሚገባ ተመዝግበው እንዲቀመጡ…


