“የመራጭነት ካርዳችንን በመውሰድ የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ዛሬ መወሰን አለብን” አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
7ተኛውን አገራዊ ምርጫን በማስመልከት በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለምርጫ በሚወዳደሩበት ወረዳ በቢዮ አዋሌ ክላስተር የምርጫ ካርዳቸውን በመመዝገብ ወስደዋል። በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ለመራጭነት መመዝገብ በሀገርዎ ጉዳይ ላይ የመወሰን ሥልጣን እንዳለን የምናረጋግጥበት መብት ነው ብለዋል። ዜጎች አገር ወዳድነታቸውን በተግባር ከሚያሳዩባቸው መንገዶች በምርጫ ንቁ ተሳታፊ መሆን አንዱ ሲሆን፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ለሀገረ መንግሥት…


