“ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ በየክልሎች የሚከናወኑ ከ17 ዓመት በታች የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በከፍተኛ ደረጃ ያነቃቃል።”:-የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ለመላዊ ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ብሄራዊ ቡድኑ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶ በመሰራቱ የተገኘ ድል መሆኑን ኮሚሽነር አለሙ ገልፀው፤ የኢትዮጵያ ከ17…


