በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የንግድ፣ የኢንደስትሪ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ስራዎችን አጠናክሮ የማስቀጠል ስራዎች ይከናወናሉ” የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ።
”በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ በነበረው የስልጠና ማጠቃለያ ላይ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሠጡት የስራ አቅጣጫዎች መሠረት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ የ100 ቀን እቅድ በድሬዳዋ አስተዳደር ተዘጋጅቶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ፤ በአስተዳደሩ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባና…


