የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን አጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ጉባኤ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን አጽድቋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ አዋጁ ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ትልቅ ሚና ያለውና የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በዕቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የተጣለ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡ አዋጁ…


