በሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለዉ የተጠናከረ እርምጃ ይጠቀምባቸዉ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማረካቸዉንና ከሽብር ቡድኑ ጋር ግንኙነት የነበራቸዉ አካላት በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል::
የድሬዳዋ አስተዳደር የፀጥታ ግብር ሀይል እንዳስታወቀዉ በድሬዳዋ ፣በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሆኑ ተጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎችን መሽሸጊያ በማድረግ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ልማትን ለማደናቀፍ ሙከራ ሲያደርግ የነበረው የሸኔ የሽብር ቡድን ላይ ባፉት ቀናት ጥምር የፀጥታ ሀይሉ ባካሄደዉ የጋራ ስምሪትና በወሰደዉ ጠንካራ እርምጃ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸዉን አስታውቋል:: ይሄዉ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ሃይል ማለትም የሀገር መከላኪያ ሰራዊት…


