የገጸ ምድር እና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶችን ለመስኖ ልማት የማዋል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል የሀገራችንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ተግባር ዋነኛው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት በመስኖ ልማት አማካኝነት ወደ ግብርና ማዕከልነት እየተቀየሩ መሆኑን ነው ያስታወቁት። ለዚህም የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ…


